KW Innocation & Technology Office

Loading

ኢኖቬሽን ለልማት፣ ቴክኖሎጂን ለለውጥ!

ዜጎችን ዘመኑ ከሚፈልገው ክህሎት ጋር ማገናኘትቴክኖሎጂዎችአጠቃቀም ክህሎት ጋር

ለወረዳ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሥራዎችን ለሕብረተሰቡ በአግባቡ በማልማት፣ በመተግበርና በማስፋት ዞናዊ ፡ ክልላዊ ብሎም አገራዊ የተወዳዳሪነት አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ነዉ፡፡ 

ዐቅም መገንባት

የሰውን ኀይል ማሠልጠን፣ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን መገንባት እና የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ማረጋገጥ

የፈጠራ (ኢኖቬሽን) እና ቴክኖሎጂ ምርምርን ማስተባበር፣ ማበረታታት እና ድጋፍ መስጠት — የወረዳችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማምጣት የሳይንስና ቴክኖሎጂ እንቅስቃሴዎችን ማስተባበር።
የዲጂታል ግንዛቤ (Digital Literacy) ማሳደግ — ለዜጎች፣ ለወጣቶች እና ለተቋማት የዲጂታል ትምህርትና ስልጠና መስጠት።
ዲጂታል ሽግግር (Digital Transformation) — የመንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታል ማድረግ (Paperless Office / E-Office)፣ የዲጂታል ኢኮኖሚን ማሳደግ እና የዲጂታል መሠረተ ልማት መገንባት።
ቢሮአችን በአጠቃላይ ወረዳውን በቴክኖሎጂና ፈጠራ የበለጸገ ለማድረግና የዲጂታል ኢኮኖሚ መገንባት ላይ ያተኮረ ነው
ሥልጠናዎቻችንን ያግኙ
ከአገልግሎቶቻችን በጥቂቱ

ከዘመኑ ጋር ለመራመድ ከኛ ጋር ይገናኙ

ጽሕፈት ቤታችን ዕውቀትን ወደ ሀብት፣ ፈጠራን ወደ ሥራ እና ቴክኖሎጂን ወደ ዘመናዊ ኢኮኖሚ በመለወጥ ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል

የመረጃ ግንዛቤ (Information Literacy)

በተለያዩ ሚዲያዎች የሚቀርቡ መረጃዎች ተአማንነታቸውና ሐቅን መሠረታ ያደርጉ መሆናቸውን በመገንዘብ ከሐሰተኛ መረጃዎች እራስን መጠበቅ የሚያስችል ሥልጠና ነው።

ሚዲያ ግንዛቤ (Media Literacy)

የሚዲያ ግንዛቤ ማለት በተለያዩ ሚዲያዎች ማለትም በሕትመት፣ ዲጂታል ወይም በብሮድካስት መልክ የሚቀርበውን መረጃ የመጠቀም፣ የመመርመር፣ የመገምገም እና የመፍጠር ዐቅም ማዳበር ማለት ነው። አንድ ሰው የሚዲያ ግንዛቤ ወይም ዕውቀት አለው የሚባለው እነዚህ ችሎታዎችን በአንድነጥ አጣምሮ የያዘ እንደሆነ ነው።

መሠረተ ልማት ዝርጋታ

ለተቋማት የሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን ማበልጸግ፣ ማሸጋገርና ለተጠቃሚዎች የክህሎት ክፍተቶችን መሙላት

ቴክኖሎጂ ግንዛቤ (Technology Literacy)

በዚህ ዘመን ለሥራና ለዕለት ዕለት ተግባራት የምንጠቀማቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለምሳሌ ኮምፕዩተርና ስልክ በአግባቡ ለተፈጠሩበት ዓላማ መጠቀም መቻልና ከአለአጋብብ መጠቀም ጋር በተያያዘ ሊያስከትሉ የሚችሉ ችግሮችን መገንዘብ
ምን አዲስ ነገር አለ!!

ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን እዚህ ያገኛሉ!

11/04/ 2026
የሚዲያ ግንዛቤ (Media Literacy) Part III

የሚዲያ ግንዛቤ መርሆች በሚዲያ የሚቀርብ ማንኛውም ሐሳብ እውነትን ለማሳየት የተጠቀሙበት ዘዴ እንጂ ነባራዊ እውነታን አያመለክትም። ወይም በአጭሩ ስለ እውነት የቀረቡ ዘገባዎች እንጂ በራሳቸው እውነት አይደሉም። ሚዲያ መሬት ላይ የሌለ ምናባዊ…

Read more
11/04/ 2026
የሚዲያ ግንዛቤ (Media Literacy) Part II

እመኑልኝ ቋንቋ (Persuasive language) የሚዲያ ትልቁ ትግል የሚተላለፈው መልእክት እውነት እንደሆነ ታዲያሚዎች እንዲያምኑ ማድረግ ነው። ለዚህ ነው ፊልሞች ላይ ወይም ማስታወቂያዎች ላይ የተለያዩ ተጨማሪ የዕይታ መሳቢያ (Visual Effects) ቴክኒኮችን የሚጠቀሙት።…

Read more